የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎትን ጎበኙ፡፡*******************ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባበተከበሩ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀላፊ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስራ ሀላፊዎች ቡድን በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በፌዴራል በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፤ የመሶብ አገልግሎት በተመለከተ በፌዴራል መሶብ አገልግሎት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ከኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ምክክር አካሂደዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የደረሰበት ደረጃ በክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌና በክብርት ወ/ሮ አልማዝ መሰለ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡ሪፎርሙ አሁን የደረሰበት ደረጃ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን የመሩት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌና የተከበሩ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢ.ኮ.ቴ. ዘርፍ ሀላፊ ናቸው፡፡ የኮሚሽኑ የካውንስል አባላትም በውይይቱ ላይ ታድመዋል፡፡በመድረኩ ላይ በአሁኑ ወቅት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርሙን ሊመሩና ሊሸከሙ የሚችሉ የተሟሉ የህግ ማእቀፎችና፣ ማስፈጸሚያ ሰትራቴጂዎች የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላትም የተሰራውን ስራ አድንቀው በውይይቱ የተነሱና በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት እንደሚቻል ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

